=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ችግረኞች አቤቱታቸውን የሚያቀርቡለት አካል ማነው? መከራ የደረሰባቸው ፍጡራን ሁሉ የሚመኩበት ፣ የሚጠጉበት እና የሚጠይቁት ምላሶች አዘውትረው የሚያዎሱት እና ልቦች የሚያመልኩት ማንን ነው? እሱ አሏህ ነው ፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም። በችግርና በደስታም ጊዜ እሱን የመማፀን ፣ በመከራ ጊዜያትም ወደ እሱ የመቃረብ እና በደጃፉ ላይ ድፍት ብለን እያለቀስን ከወንጀሎቻችን መሃርታን እየጠየቅን እሱን የመለመን ሐቅም አለብን። የዚያኔ ችሮታው ይመጣል ፣ እርዳታውም ይደርሳል ፣ መድህኑም በፍጥነት ይገኛል።
-<({አል-ቁርአን 27:62})>-
«ችግረኛ በለመነው ጊዜ መልስ የሚሰጥ ከአሏህ ሌላ ማን አለ?»
ሊሰምጥ የነበረውን ያድናል ፤ የጠፋውን ይመልሳል ፤ የተፈተነውን ይደርስለታል ፤ የተበደለውን ይረዳል ፤ የጠመመውን ያቃናል ፤ የታመመውንም ያሽራል ፤ መከራ የደረሰበትን መከራውን ያነሳለታል።
-<({አል-ቁርአን 29:65})>-
«በመርከቦች ውስጥ በተሳፈሩ ጊዜ አሏህን መገዛትን ለርሱ ብቻ ያጠሩ ሲሆኑ ይጠሩታል።»
አሁን የሃዘን ፣ የጭንቅ ፣ የትካዜና የችግር ማላቀቂያ ዱአዎችን ፀሎቶችን አልዘረዘርልህም። ባይሆን ከሱ ጋር መልካም ንግግርን ታውቅ ዘንድ አውቀህም ትጠራው ፣ ትለምነውና ትማፀነው ዘንድ የሱና መፅሐፎችን እጠቁምሃለሁ። እርሱን ካገኘኸው ሁሉን ነገር አግኝተሃል። በሱ ኢማንን ፅኑ እምነትን ካጣህ ደግሞ ሁሉን ነገር አጥተሃል። ጌታህን መለመንህ እራሱን የቻለ አምልኮ ነው። የምታጣውን ከማግኘትህም የበለጠ የመታዘዝ ምልክት ነው። አሳምሮ የዱዓእ አደራረግ ዘዴን የሚያውቅ ሰው ባይተክዝ ባይጨነቅ እና ባይቸገርም ይገባዋል። የእርሱ የአሏህ ገመድ ሲቀር ሁሉም ገመዶች ይቆረጣሉ። ሁሉም በሮችም ይዘጋሉ የሱ በር ሲቀር። እሱም ቅርብ ፣ ሰሚ ፣ መልስ ሰጭ ሲሆን ችግረኛ በጠራው ጊዜ መልስ ይሰጣል። አንተ ድሃ ፣ ደካማና ችግረኛ ስትሆን እሱ ደግሞ ባለሃብት ፣ ሃያልና ብቸኛ እንዲሁም ሁሉን ቻይ በመሆኑ ትለምነው ዘንድ ያዝሃል።
-<({አል-ቁርአን 40:60})>-
«ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላችኋለሁና።»
መከራዎች ቢደርሱብህ እና ችግሮች ቢያጋጥሙህ እሱን አብዝተህ አውሳው። የነፃነት ዘውድን ታገኛለህና ስሙን በመቀደስ በግንባርህ ተደፋ። ተዋረድለት እሱን በማምለክ የመድህን ኒሻን ትሸለማለህ። እጅህን ዘርጋ ፤ መዳፎችህን ከፍ አድርግ ፤ ምላስህን ልቀቅ ፤ አብዝተህ ጠይቀው ፤ ችክ ብለህ ለምነው ፤ በሩን ተመላልሰህ አንኴኴ ፤ እዝነቱን ተጠባበቅ ፤ እርዳታውን ከጅል ፤ ስሙን አውሳ ፤ በሱ ያለህን እምነት አጠንክር ፤ ወደ እሱ ተጠጋ ያለማቇረጥ ተገዛው ትድናለህ ትደሰታለህም።
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
|
---|